Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ
  • 3.8

Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ

  • Latest Version
  • ብራና አፕስ Birana Apps
Advertisement

The first complete Ethiopian Othodox Bible in Geez, Amharic and English.

About this app

በይዘቱ ተሟልቶ በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የተዘጋጀ የመጀመሪያው ምሉዕ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ደንብ ጠብቆ የተዘጋጀ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዲሁም የቀኖና መጻሕፍት ብላ በ1962 ዓ.ም ያሳተመችውን መጽሐፍ ቃል በቃል ለቅሞ መዝግቧል።

መጽሐፉ ለሃይማኖት አባቶች ለሰባክያነ ወንጌልና ለመምህራን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ በሚሰማሩበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው መያዝ ሳይኖርባቸው በቀላሉ ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል:: ምዕመናንም የግዕዙንና የአማርኛውን ትርጉም ምሥጢሩ ሳይዛባ በስልካቸው እንዲጠቀሙ ይረዳል::

የመጽሐፉ ልዩ ባሕርያት
•tሰማንያ አንድ (81) መጻሕፍትን ያካተተ ነው።
•tሙሉ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በግዕዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ነው።
•tየአማርኛው ትርጉም በጥንታዊው የአባቶቻችን አጻጻፍና አገላለጽ ሃይማኖታዊ ለዛውን ሳይለቅ የተጻፈ ነው።
•tየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸውን የብሉይና የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍትን ያካተተ ነው።
•tፊደሉና አጻጻፉ በግእዝና በአማርኛ መዛግብተ ቃላት መሠረት ታርሞ የተዘጋጀ ነው።
•tየፊደሎችን መጠን በቀላሉ ማስተካከያ መንገድ አለው።
•tበቀንና በጨልማ ለማንበብ የራሱ ማስተካከያ ተካቶበታል።
•tማስታወሻ መያዣ፣ ማቅለሚያ፣ ዕልባት ማድረጊያ ተካቶበታል።
•tማጣቀሻዎች በየቁጥሩ የተካተቱ ሲሆን በቀላሉ አንድ ጊዜ ብቻ ጠቅ በማድረግ ገጹን ሳይለቁ ማንበብ ያስችላል።
•tበጣም ፈጣንና የፍለጋ ውጤቶችን በማቅለምና በቁጥር የሚያሳይ መፈለጊያ ተካቶበታል።
•tየአማርኛ፣ የግእዝና የእንግሊዝኛ ዕትሞችን ጎን ለጎን፣ መስመር በመስመር ፣ ከላይና ከታች አድርገን ለማንበብ ያስችላል።
•tየመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በአኅጽሮት ወይም በሙሉ ስም ለመዘርዘር ማስተካከያ ተደርጎበታል።
•tየፊደል መጠኑን በቀላሉ ማሳነስና ማሳደግ የሚያስችል ማስተካከያ ተካቶበታል።
•tየመጽሐፍ ቅዱስ መስመሮችን እንድፍላጎትዎ ማስተካከል ይችላሉ።
•tከዚህ በፊት ያነበቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከዚህ በፊት የተነበቡ በሚለው ስር ያገኟቸዋል።
•tየተለያዩ ቋንቋዎችን በመጠቀም የመጽሐፉን ይዘት መተርጎም ይችላሉ።

ከ66ቱ መጻሕፍት በተጨማሪ 19 የብሉይ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት እና 8 የአዲስ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍትን በግእዝና በአማርኛ አሟልቶ ተዘጋጅቷል ።

የብሉይ ኪዳን ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት
1.tመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል
2.tመጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ
3.tመጽሐፈ ጦቢት
4.tመጽሐፈ ዮዲት
5.tመጽሐፈ አስቴር
6.tመጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ፣ ካልእና ሣልስ
9.tመጽሐፈ ሲራክ
10.tጸሎተ ምናሴ
11.tተረፈ ኤርሚያስ
12.tሶስና
13.tመጽሐፈ ባሮክ
14.tመጽሐፈ ጥበብ
15.tመዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ
16.tተረፈ ዳንኤል
17.tመጽሐፈ ኩፋሌ
18.tመጽሐፈ ሔኖክ
19. መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን


የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት

⒈ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
⒉ መጽሐፈ አብጥሊስ
⒊ ግጽው ዘሲኖዶስ
⒋ ሥርዓተ ጽዮን
⒌ መጽሐፈ ዲድስቅልያ
⒍ መጽሐፈ ትእዛዝ
⒎ መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ እና ካልእ

ያውርዱና ብዙ የተደከመበትን መጽሐፍ ቅዱስ በእጅዎ ያስገቡ።

Versions Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ